አሶሳ ዩኒቨርሲቲ  ከአስር የክልል ሴክተር  መስሪያቤቶች  ጋር  የጋራ የመግባቢያ ሰነድ  ተፈራረመ

ዩኒቨርሲቲው ሰኔ 15/2ዐዐ9 ዓ/ም ከክልሉ ሴክተር መስሪያቤቶች ጋር በጋራ ለመስራት እንዲችል የውል ስምምነት / Memorandum of understanding/ ተፈራርሟል፡፡

 

በበጀት ዓመቱ ጥሩ የስራ አፈፃፀም ስመዘገቡ ሰራተኞች እውቅና ተሰጠ

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በ22/11/ዐ9 ዓ.ም በ2ዐዐ9 የበጀት ዓመት ጥሩ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የአስተዳደር ሰራተኞች ፣ መምህራን ፣ የት/ት ክፍል ሀላፊዎች ፣ አስተባባሪዎች ፣ ቡድን መሪዎች እና መካከለኛ አመራሮች የምስክር ወረቀትና የገንዘብ ሽልማት አበረከተ፡፡

ያንብቡት…

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በክልሉ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የማጠናከሪያ ት/ት በመስጠት ላይይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሀምሌ ወር 2ዐዐ8 ዓ.ም በሶስቱም ዞኖች ለተውጣጡ በክልሉ የሚገኙ ተማሪዎችን ከክልል ት/ት ቢሮ ጋር በመሆን ምልመላውን ካደረገ በ|ላ ትምህርቱን በመስጠት ነበር ይህን የክረምት የመጠናከሪያ ፕሮግራም የጀመረው፡፡

ያንብቡት…

FH ኢትዮጵያ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳለዉገለፀ

ሀምሌ 29/2ዐዐ9 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፤የግብርናና የተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ መምህራን፣ የአልሙናይ ኢንዱስትሪ ትስስር እና የፋርም ዳይሬክቶሬቶች እና ባለሙያዎች በተገኙበት በባምባሲ ወረዳ ባሉ ሁለት ቀበሌዎች ላይ FH ኢትዮጵያ በሰጣቸዉ ስልጠና መሰረት የቁጥብ እርሻ ልማትን ተገባራዊ ያደረጉ አርሶ አደሮች ማሳ ጉብኝት አድርጓል፡፡ 

ያንብቡት…

The Universiyty Provides Deliverology Training for all Level Leaders
The Universiyty provided one day training for the presidents, College Deans , directors ,coordinators and department heads on August 15/2009 E.C. The objective of the training was to introduce the new concept of deliverology, higher education targets on deliverology as well as what is planning in deliverology and how it implements.
read more...

Assosa University’s Bamboo seedling plantation

The month of August is the commemorating month of the late Prime Minister Meles Zenawi death in the country level.

የዉጭና ህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ዋና ዋና ተግባራት

ዋናዋናተግባራት

 1. ፕሬዘዳንቱን እና  ከፍተኛ ሃላፊዎችን በማማከር ዉጫዊ ግንኝነቶችን የሚመለከቱ እቅዶችን ያዘጋጃል፡፡
 2. የህዝብ ግንኙነት ፕሮግራሞችን ይተገብራል፣ የግንኙነቱ ስራ የዩኒቨርስቲዉን ራዕይና ተልኮ የሚያንፀባርቅ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ በሀገር ዉስጥ እና በዉጭ ሀገር ዉጤታማ የሆነ ግንኙነት መረብ ይዘረጋል፡፡

  ዝርዝርተግባራት

 1.  ጠንካራ የሆነ የዩኒቨርስቲዉን ምስል የሚያጎላ ግንኙነት ይገነባል፡፡ በዉጭ እና በሀገር ዉስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ጋር አዲስ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፡፡
 2.  ዉጫዊ የሆኑ የምርምር እስኮላርሽፕ ፕሮግራሞችንበሚመለከትመረጃ ይሰጣል፡፡
 3. ከኢንስቲቲዮቶችና ፕሮጀክቶች ጋር ዉጫዊና ወቅታዊ የሆኑ ግንኙነቶችን ይመሰርታል፡፡ በዩኒቨርስቲዉ ከሚገኙ በርካታ የስራ ክፍሎች ጋር የጎንዮሽ ግንኙነት በመመስረት ይሰራል፡፡
 4. አዲስ የሚመጡ ተማሪዎችን ለመቀበል በሚዘጋጁ የእንኳን ደህና መጣችሁ ስነስርዓቶችን ያስፈፅማል፡፡
 5.  አለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ጉብኝቶችን እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች ያስፈፅማል፡፡
 6. ትምህረታዊ የማስታወቂያ ስራዎች እንደ ድሀረ-ገጽን በተመለከተ ከኮንትራክተሮች ጋር የሚደረጉ ስምምነቶችን ያስተባብራል፡፡በድህረ-ገጽ የሚወጡ ጹሁፎች ይዘትን የማስታወቂያ ስራዎችን እና በየሶስት ወሩ የሚታተመዉ የዜና መጽሄት ስራ ላይየአርትኦት ስራ ያከነዉናል፣ ይሰራል፡፡
 7. ዩኒቨርስቲዉን ሊያስተዋዉቁ የሚችሉ ወቅታዊ የማስተወቂያስራ ላይ  ይሳተፋል፣ የአርትኦት ስራ ያከናዉናል፣ ይሰራል፡
 8. ዩኒቨርስቲዉን ሊያስተዋዉቁ የሚችሉ ወቅታዊ የማስተወቂያስራዎችን ይገመግማል፣ የማስተካከያ ሀሳቦችን ያቀርባል ፡፡
 9. ለትምህርት መርሃ ግብሮች፣ ለዩኒቨርስቲዎች ራዕይና ተዕልኮ ፣ ለማህበራዊ ሃላፊነቶች አንዲሁም ለስፖርታዊ እና ባህላዊ ክንዋኔዎች መሳካት ከለላ እና ድጋፍ ይሰጣል፡፡
 10. በዩኒቨርስቲዉ የቢዝነስ እድገትና ስኬት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ልምዶች እና አዳዲስ ሀሳቦችን በመለየት ዉጫዊ የሆነ ተከታታይ ግምገማ ያካሄዳል፡፡
 11. የረጅም ግዜ ተቋማዊ ለዉጥ ሊያስከትሉ የሚችሉ ቀጣይነት ያላቸዉ የገቢያ ጥናቶች እና የህዝብ አስተያየትን ያካተቱ ምርምሮችን በዋና ዋና የተመረጡ አካባቢዎች ላይ በማተኮር ጥናት ያደርጋል፡፡
 12. በዩኒቨርስቲዉ ዋና ዋና ታርጌት ኦዲያንስ መካከል የዉጫዊ እና የዉስጣዊ ገቢያ ጥናት ያካሄዳል፡፡
 13. እቅድ ያዘጋጃል፣ የተመደበለትን በጀት ያዛል በትክክል ስራላይ መዋሉን ይከታተላል፣ የስታፍ ኦፕሬይዛል ያደራጃል ቀጥተኛ በሆነ መልኩ ተገቢ የሆኑ የስታፍ ግንኙነት ይመሰርታል
 14. ሌሎች ከፕሬዝዳንቱ የሚሰጡ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

 

Externaland Public Relations Office

Background

As part of its mandate, our University’s External and Public Relations Office is a pillar of the university and works closely with the University’s academic and administration staff, and students. EPRO is committed to develop communication strategies for the distribution of academic wise contents and research works through local, national and international news media as well as via online social networks.

The Office is also responsible to create the communication channel between Assosa University (AsU) and the public. It proactively informs the media (print, voice, TV), supports and consults the Managing Council and the Deans in public relations aspects.

External and Public Relations Office will work with individual Faculty and departments and administration area to build a strategic communications plan to increase awareness and visibility of the research, expertise, accomplishments and mission and vision of AsU.

The Office strives to build a positive image of AsU in the public opinion and supports the President in international communication, fund raising endeavors and alumni relations. It jointly works with the University’s managing council and creates a corporate identity and a corporate design of activities with various work processes and units.

The General Objective of EPRO:

 • To establish effective and smooth local and international relations and provide current information so as to enhance the transformational activities of AsU in its endeavor to become the Idol of excellence in science and technology.

Sub Objectives:

 • To promote and build academic excellence into every process of the University; ranging from Faculty to department level and strengthen AsU’s local and external relations on the basis of the core values and principles of the University.
 • To provide necessary and accurate information available to academic and administrative staffs and students to facilitate informed decision making in very important issues.
 • To facilitate cooperation and collaborations with various local and international universities and organizations for strong partnership.

 What we do

 • Maintain internal and external communications of AsU and create links with local and international universities;
 • Provide general information about the services offered by the University such as teaching, research, community services and administrative procedures to customers
 • Prepare listening point for any claims, suggestions or comments regarding the University;
 • Edit AsU's annual report, prepare and distribute magazines, newsletters, brochures and flyers, hold press conferences, take care of media releases, get access to the University website and supervise and update the official website of the University regularly;
 • Facilitate custom clearance issues for donations delivered from foreign countries,
 • Facilitate the issuance of visa and residence ID card for expatriate staffs;
 • Organize and facilitate local and international conferences, seminars, workshops and arranges media releases;  

 

 

Contact

kefyalew Abdissa (Assistant professor)=Head of Public and International relation Office.

   

Telephone=+251577750784

e.mail=Kefyalew Abdissa < This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. >

 

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሥዕል አዉደ ርዕይ አካሄደ

ዩኒቨርሲቲዉ ከሰኔ 03-05/2009ዓ/ም በባንቡ ፓራዳይዝ ሆቴል ለ2ኛ ጊዜ ለእይታ ያቀረበዉ የሥዕል አዉደ ርዕይ የምረቃ በዓል ያደረገ ሲሆን ሥራዎቹ በፒካሶ የሥዕል አርት ክለብ በሰዓሊ ፋሲል ሙሉጌታ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ፈጠራና ባህል ማዕከል ዳይረክቶሬት ጋር በመተባበር የተሠሩ መሆኑን መገንዘብ ተችለዋል፡፡

የተሰሩት ሥዕሎች በከፊል
አዉደ ርዕዩን የከፈቱት የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሀይማኖት ዲሳሳ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲዉ እንደዚህ አይነት ልዩ ችሎታ ያላቸዉን ተማሪዎች ማጠናከርና እዉቅና መስጠት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዉ ወደ ፊትም ዩኒቨርሲቲዉ ከጎናቸዉ እንደሚቆም ቃል ገብተዋል፡፡ የተሠሩት የሥዕል ሥራዎቹም ጥሩና አበረታች መሆናቸዉን ጭምር ተናግረዋል፡፡

 

ሰዓሊዉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የመካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ ሲሆን ወደዚህ ሙያ የተቀላቀለዉ የ2ኛ ዓመት ተማሪ እያለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ተማሪዉ እስካሁን ለዚህ ሥራ በግሉ ከ ብር 10,000 በላይ እንዳወጣና ለኪነ-ጥበቡ እድገት የዩኒቨርሲቲዉ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡ ይህንን አኩሪ ሥራ ራሱ ባቋቋመዉ ‘’ፒካሶ የሥዕል አርት ክለብ’’ ከሥሩ 750 አባላት በላይ በማሰለፍ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተማሪዉ ጨምሮ ገልፀዋል፡፡ 

ተመልካቹ የሥዕል ሥራዎቹን ሲጎበኙ
አንዳንድ አስተያዬት ሰጪዎች በተማሪ ፋሲል ሙሉጌታ የተሰሩት የሥዕል ሥራዎችን አድንቀዉ ይበልጥ ለማጠናከር የዩኒቨርሲቲዉ ድጋፍ ወሳኝ መሁኑን ገልፀዉ ዩኒቨርሲቲዉ የአርት (ኪነ-ጥበብ) ትምህርት ቤት ቢከፈትላቸዉ ከዚህ የበለጠ መስራት እና ብዙ ተከታዮችን ማፍራት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

  

በአዉደ ርዕይዉ የተሳተፉት አስተያዬት ሲሰጡ