አሶሳ ዩኒቨርሲቲ  ከአስር የክልል ሴክተር  መስሪያቤቶች  ጋር  የጋራ የመግባቢያ ሰነድ  ተፈራረመ

ዩኒቨርሲቲው ሰኔ 15/2ዐዐ9 ዓ/ም ከክልሉ ሴክተር መስሪያቤቶች ጋር በጋራ ለመስራት እንዲችል የውል ስምምነት / Memorandum of understanding/ ተፈራርሟል፡፡

 

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የአድት አገልግሎትን በተመለከተ ስልጠና ተሰጠ 

በአሶሶ የኒቨርሲቲ  ለሁለት ተከታታይ ቀናት ከግንቦት 25/2009-26/2009 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው የውስጥ ኦዲት ከትምህርት ሚኒስተር የኦዲት ባለሙያ በማስመጣት ስልጠናውን ሰጥቷል፡፡
በስልጠናው ላይም የዩኒቨርሲቲው  ከፍተኛ አመራሮች እና መካከለኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡ በዕለቱም የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሀይማኖት ደሲሳ የስልጠናው ተሳታፊዎችን ስልጠናውን ትኩረት ሰጥተው እንዲከታተሉ እና  በእለት ተለት ስራዎቻቸው ላይ ተግባራዊ እንድያደርጉ በማሳሰብ ነበር ስልጠናው የተጀመረው፡፡

 
                                                         ዶ/ር ሀይማኖት ዲሳሳ መክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ

ስልጠናውን የሰጡት  የትምህርት ሚኒስተር የዉስጥ ኦዲት  አገልግሎት ዳ/ር አቶ መኮነን ጨንጫ ሲሆኑ የስልጠናው  አብይ ትኩረትም በመንግስት የፋይናንስ  አስተዳደር መመሪያ ፣የግዠ እና ንብርት አስተዳደር መመሪያዎችን እና ስለ ሰው ሀብት ስራ አመራር ተግባራት እንድሁም መሰረታዊ የሲቪል ሰርቪስ ህጎች ዙሪያ በጥልቅ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ከሚተገበሩት ተጨባጭ አሰራሮች ጋር በማነፃጸርውይይት ተደርጓል፡፡                                                 አቶ መኮነን ጨንጮ ሲያሰለጥኑ

 ሁሉም  የስልጠናው ተሳታፊዎችና  የዩኒቨርሲቲው  ከፍተኛ አመራሮች ከዚህ በኃላ ለምንሰራቸው ስራዎች ሁሉ መመሪያ እና አዋጆችን መሰረት በማድረግ መስራት እንደሚገባ የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ ምክንያታዊ መሆን ካለብን በህግ ብቻ መሆን እንደሚኖርብንና በ2010ዓ/ም ዜሮ የኦድት ግኝት ለማስመዝገብ ሁሉም የስራ ክፍሎች መመሪያን መሰረት በማድረግ መስራት አማራጭ የሌለው መሆኑን ተስማምተዋል፡፡  

                                                                   

 

                                                 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሥዕል አዉደ ርዕይ አካሄደ

ዩኒቨርሲቲዉ ከሰኔ 03-05/2009ዓ/ም በባንቡ ፓራዳይዝ ሆቴል ለ2ኛ ጊዜ ለእይታ ያቀረበዉ የሥዕል አዉደ ርዕይ የምረቃ በዓል ያደረገ ሲሆን ሥራዎቹ በፒካሶ የሥዕል አርት ክለብ በሰዓሊ ፋሲል ሙሉጌታ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ፈጠራና ባህል ማዕከል ዳይረክቶሬት ጋር በመተባበር የተሠሩ መሆኑን መገንዘብ ተችለዋል፡፡

የተሰሩት ሥዕሎች በከፊል
አዉደ ርዕዩን የከፈቱት የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሀይማኖት ዲሳሳ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲዉ እንደዚህ አይነት ልዩ ችሎታ ያላቸዉን ተማሪዎች ማጠናከርና እዉቅና መስጠት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዉ ወደ ፊትም ዩኒቨርሲቲዉ ከጎናቸዉ እንደሚቆም ቃል ገብተዋል፡፡ የተሠሩት የሥዕል ሥራዎቹም ጥሩና አበረታች መሆናቸዉን ጭምር ተናግረዋል፡፡

 

ሰዓሊዉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የመካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ ሲሆን ወደዚህ ሙያ የተቀላቀለዉ የ2ኛ ዓመት ተማሪ እያለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ተማሪዉ እስካሁን ለዚህ ሥራ በግሉ ከ ብር 10,000 በላይ እንዳወጣና ለኪነ-ጥበቡ እድገት የዩኒቨርሲቲዉ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡ ይህንን አኩሪ ሥራ ራሱ ባቋቋመዉ ‘’ፒካሶ የሥዕል አርት ክለብ’’ ከሥሩ 750 አባላት በላይ በማሰለፍ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተማሪዉ ጨምሮ ገልፀዋል፡፡ 

ተመልካቹ የሥዕል ሥራዎቹን ሲጎበኙ
አንዳንድ አስተያዬት ሰጪዎች በተማሪ ፋሲል ሙሉጌታ የተሰሩት የሥዕል ሥራዎችን አድንቀዉ ይበልጥ ለማጠናከር የዩኒቨርሲቲዉ ድጋፍ ወሳኝ መሁኑን ገልፀዉ ዩኒቨርሲቲዉ የአርት (ኪነ-ጥበብ) ትምህርት ቤት ቢከፈትላቸዉ ከዚህ የበለጠ መስራት እና ብዙ ተከታዮችን ማፍራት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

  

በአዉደ ርዕይዉ የተሳተፉት አስተያዬት ሲሰጡ


Copyright © 2016. All Rights Reserved.