አሶሳ ዩኒቨርሲቲ  ከአስር የክልል ሴክተር  መስሪያቤቶች  ጋር  የጋራ የመግባቢያ ሰነድ  ተፈራረመ

ዩኒቨርሲቲው ሰኔ 15/2ዐዐ9 ዓ/ም ከክልሉ ሴክተር መስሪያቤቶች ጋር በጋራ ለመስራት እንዲችል የውል ስምምነት / Memorandum of understanding/ ተፈራርሟል፡፡

 

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የእግር ኳስ የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ

ዩኒቨርሲቲዉ ከሚያዚያ 17-29/2009ዓ.ም የስፖርት ሳይንስ ትም/ት ክፍል ከአሶሳ ዞንና ማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ ለተዉጣጡ ባለሙያዎች የእግር ኳስ የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ፡፡

ሰልጠናዉን  በይፋ የከፈቱት የምርምርና  ማህበረሰብ  አገልግሎት ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር  መ/ር ተፈራ ተሾመ ሲሆኑ ዩኒቨርሲቲያችን ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን  የምርምርና ማህበረሰብ  አገልግሎት  ስራዎችን  እየሰጠ  ይገኛል ፡፡ከእነዚህም መካከል እስካሁን አስራ አንድ የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን ለተለያዩ የዩኒቨርሲቲው እና የክልሉ ማህበረሰብ የሰጠ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት  ፀድቆ ወደ ተግባር የገባዉ  የአራት ዓመት የስፖርት  ፕሮጀክት  ስልጠና መጀመሩን ይፋ አድርገዋል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ  ሰልጣኞች በቆይታቸዉ  ተገቢውን እዉቀትና  ክህሎት በመቅሰም  ተተኪ ታዳጊዎችን  ማፍራት እንደሚጠበቅባቸዉ  በማስገንዘብ  ስልጠናዉን በይፋ ከፍተዋል፡፡

ስልጠናዉ ያተኮረባቸዉ  ነጥቦች  ተተኪ ስፖርተኞችን  እንዴት ማፍርት ይቻላል?  ኳስን እንዴት  መቆጣጠር ይቻላል? የምናሰለጥናቸዉን ታዳጊዎች ስነ-ልቦና መረዳት እና ከወላጆቻቸዉ ጋር በመተማመን በፕሮጀክቱ የሚታቀፉ ሰልጣኞችም እድሜ ከ13 ዓመት በታች  መሆን እንዳለበት ለሰልጣኞች ግንዛቤ እንዲይዙ በማድረግ የስልጠናዉ ሂደትም ንድፈ ሐሳብን  ከተግባር ጋር ያጣመረ እንዲሆን ስልጠናዉን የሰጡት አካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቴር እና የስፖርት ሳይንስ መምህር አበራ ባይሳ  ገልፀዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ በዉል  ስምምነታቸዉ መሠረት  ስልጠናዉን ወስዶ  የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ  ሶስት ወረዳዎች  በፕሮጀክቱ  የሚቀጥሉ  ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ  ብቁ የሆኑ ታዳጊዎችን  በስፖርቱ ዘርፍ በማሰልጠን ረገድ የራሳችሁን  አሰተዋፅኦ በማበርከት እንዲሁም  በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎችም  ተተኪዎችን  ከማፍራት አንፃር ሙያዊ ግዴታቸዉን  መወጣት እንዳለባቸዉ  ዳይሬክተሩ  ጠቁመዋል፡፡

ሰልጣኞችም  በሰጡት አሰተያየት  ስልጠናዉ ከአሁን በፊት  የነበረባቸውን  የግንዛቤ ክፍተት    የቀረፈላቸው  መሆኑን  ገልፀዋል፡፡ በተለይም አሶሳ ዩኒቨርሲቲ  ይህንን  የእግር ኳስ ፕሮጀክት  ስልጠና  አዘጋጅቶ  እንድንወስድ  ማድረጉ  ከክልሉም አልፎ  ለሀገር ጠቀሜታዉ የጎላ ነዉ ብለዋል፡፡ሰልጠናዉ  በተግባር ልምምድ የታገዘ  መሆኑ የበለጠ  ግንዛቤ  እንደፈጠረላቸዉም   ሰልጣኞች  ተናግረዋል፡፡

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሥዕል አዉደ ርዕይ አካሄደ

ዩኒቨርሲቲዉ ከሰኔ 03-05/2009ዓ/ም በባንቡ ፓራዳይዝ ሆቴል ለ2ኛ ጊዜ ለእይታ ያቀረበዉ የሥዕል አዉደ ርዕይ የምረቃ በዓል ያደረገ ሲሆን ሥራዎቹ በፒካሶ የሥዕል አርት ክለብ በሰዓሊ ፋሲል ሙሉጌታ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ፈጠራና ባህል ማዕከል ዳይረክቶሬት ጋር በመተባበር የተሠሩ መሆኑን መገንዘብ ተችለዋል፡፡

የተሰሩት ሥዕሎች በከፊል
አዉደ ርዕዩን የከፈቱት የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሀይማኖት ዲሳሳ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲዉ እንደዚህ አይነት ልዩ ችሎታ ያላቸዉን ተማሪዎች ማጠናከርና እዉቅና መስጠት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዉ ወደ ፊትም ዩኒቨርሲቲዉ ከጎናቸዉ እንደሚቆም ቃል ገብተዋል፡፡ የተሠሩት የሥዕል ሥራዎቹም ጥሩና አበረታች መሆናቸዉን ጭምር ተናግረዋል፡፡

 

ሰዓሊዉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የመካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ ሲሆን ወደዚህ ሙያ የተቀላቀለዉ የ2ኛ ዓመት ተማሪ እያለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ተማሪዉ እስካሁን ለዚህ ሥራ በግሉ ከ ብር 10,000 በላይ እንዳወጣና ለኪነ-ጥበቡ እድገት የዩኒቨርሲቲዉ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡ ይህንን አኩሪ ሥራ ራሱ ባቋቋመዉ ‘’ፒካሶ የሥዕል አርት ክለብ’’ ከሥሩ 750 አባላት በላይ በማሰለፍ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተማሪዉ ጨምሮ ገልፀዋል፡፡ 

ተመልካቹ የሥዕል ሥራዎቹን ሲጎበኙ
አንዳንድ አስተያዬት ሰጪዎች በተማሪ ፋሲል ሙሉጌታ የተሰሩት የሥዕል ሥራዎችን አድንቀዉ ይበልጥ ለማጠናከር የዩኒቨርሲቲዉ ድጋፍ ወሳኝ መሁኑን ገልፀዉ ዩኒቨርሲቲዉ የአርት (ኪነ-ጥበብ) ትምህርት ቤት ቢከፈትላቸዉ ከዚህ የበለጠ መስራት እና ብዙ ተከታዮችን ማፍራት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

  

በአዉደ ርዕይዉ የተሳተፉት አስተያዬት ሲሰጡ


Copyright © 2016. All Rights Reserved.