አሶሳ ዩኒቨርሲቲ  ከአስር የክልል ሴክተር  መስሪያቤቶች  ጋር  የጋራ የመግባቢያ ሰነድ  ተፈራረመ

ዩኒቨርሲቲው ሰኔ 15/2ዐዐ9 ዓ/ም ከክልሉ ሴክተር መስሪያቤቶች ጋር በጋራ ለመስራት እንዲችል የውል ስምምነት / Memorandum of understanding/ ተፈራርሟል፡፡

 

በበጀት ዓመቱ ጥሩ የስራ አፈፃፀም ስመዘገቡ ሰራተኞች እውቅና ተሰጠ

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በ22/11/ዐ9 ዓ.ም በ2ዐዐ9 የበጀት ዓመት ጥሩ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የአስተዳደር ሰራተኞች ፣ መምህራን ፣ የት/ት ክፍል ሀላፊዎች ፣ አስተባባሪዎች ፣ ቡድን መሪዎች እና መካከለኛ አመራሮች የምስክር ወረቀትና የገንዘብ ሽልማት አበረከተ፡፡

ያንብቡት…

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በክልሉ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የማጠናከሪያ ት/ት በመስጠት ላይይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሀምሌ ወር 2ዐዐ8 ዓ.ም በሶስቱም ዞኖች ለተውጣጡ በክልሉ የሚገኙ ተማሪዎችን ከክልል ት/ት ቢሮ ጋር በመሆን ምልመላውን ካደረገ በ|ላ ትምህርቱን በመስጠት ነበር ይህን የክረምት የመጠናከሪያ ፕሮግራም የጀመረው፡፡

ያንብቡት…

FH ኢትዮጵያ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳለዉገለፀ

ሀምሌ 29/2ዐዐ9 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፤የግብርናና የተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ መምህራን፣ የአልሙናይ ኢንዱስትሪ ትስስር እና የፋርም ዳይሬክቶሬቶች እና ባለሙያዎች በተገኙበት በባምባሲ ወረዳ ባሉ ሁለት ቀበሌዎች ላይ FH ኢትዮጵያ በሰጣቸዉ ስልጠና መሰረት የቁጥብ እርሻ ልማትን ተገባራዊ ያደረጉ አርሶ አደሮች ማሳ ጉብኝት አድርጓል፡፡ 

ያንብቡት…

The Universiyty Provides Deliverology Training for all Level Leaders
The Universiyty provided one day training for the presidents, College Deans , directors ,coordinators and department heads on August 15/2009 E.C. The objective of the training was to introduce the new concept of deliverology, higher education targets on deliverology as well as what is planning in deliverology and how it implements.
read more...

Assosa University’s Bamboo seedling plantation

The month of August is the commemorating month of the late Prime Minister Meles Zenawi death in the country level.

 

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች የሥራ ፈጠራ ሥልጠና ሰጠ

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ፈጠራና ባህል ማዕከል ዳይሬክቶሬት ለአሶሳ ፖሊ ተክኒክ ኮሌጅ የ2011 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች በሥራ ፈጠራና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከግንቦት 29/ 2011 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

የሥልጠናዉም ዓላማ የኮሌጁ የ2011 ዓ.ም ምሩቃን ተማሪዎች በሥራ ፈጠራ ዙሪያ ግንዛቤ ኖሯቸዉ ከመንግሥት እጅ ጠባቂነት የራሳቸዉን ሥራ መፍጠር እንዲችሉ ለማበረታታት መሆኑን የዩኒቨርሲቲዉ የሥራ ፈጠራና ባህል ማዕከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መ/ር እልፍነህ ከባሞ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተናግረዋል፡፡ አክለዉም ሥልጠናዉ የኮሌጁ ተማሪዎች በሚመረቁበት ወቅት ላይ መሰጠቱ እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ገልፀዉ ሰልጣኞቹ በሥልጠናዉ የሚሰጡ ርዕሶች ዙሪያ በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸዉ አሳስበዋል፡፡

በሥልጠናዉም የሥራ ፈጠራ ምንነት፣ የቢዚነስ ዕቅድ አዘገጃጀት፣ የሒሳብ አያያዝ እና የደንበኞች አያያዝ የሚሉ ርዕሶች ዙሪያ ዩኒቨርሲቲዉ መምህራን ሰፊ ገለጻና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡ ሥልጠናዉ በተግባር ልምምድም ጭምር የታገዘ በመሆኑ ሠልጣኞች ጥሩ ግንዛቤ መጨበጣቸዉን ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም ዩኒቨርሲቲዉ በሥራ ፈጠራ ዙሪያ ተከታታይ ሥልጠናዎችን ቢሰጥ ብዙ ስራ አጥ ወጣቶች በዘርፉ ተጠቃሚ ልያደርግ እንደሚችል ሀሳባቸዉን ሰንዝረዋል፡፡ Assosa University successfully hosted the 5th Annual National research Conference

 

 

 

In this 5th Annual National Research Conference Scholars, Keynote speakers, researchers from different universities regional stockholders, selected students and directors participated. The conference was organized from May 24-25/2019 under the grand theme of “Research for National unity and sustainable development

Dr. Haimanot Disassa, acting president of ASU delivered his well come speech and he said, We hosted four effective research conferences in the last 4 years. From these conferences we had obtained many experience but the research findings wouldn’t solve the community life. In this year we set out the theme Research for national unity and sustainable Development in order to find a solution for the National unity problem and to construct common national unity sense, he said. The acting president added the University has developed research and Community service directives since it established and it accomplished many effective activities in research and Community service. Finally, well come to Assosa town the home land of Ethiopia grand Renaissance Dam and the land of sweat Mango ,he said for the participants.

Next to this Mr. Oumer Ahmed, the university administrative board vice Chairman, the Mayor of Assosa town addressed his opening speech. He expressed his hope that the conference will finds a solution for National unity problems. After that the keynote speaker prof.Yalew Endawek from Bahir Dar University focusing on social transformation .The society can transform if only there is common understanding am0ong us, he said in his keynote speech. In addition to this, Dr Admassu Ashebr, from Addis Ababa University presented his keynote speech concerning about national unity. 

Then after, from 42 expected papers 31 papers presented, 17Universities researchers participated. From this presentation many outstanding lessons gained and experiences shared; in parallel session multidisciplinary issue were raised and addressed.

Lastly, at the general discussion participants the hospitality you received us is very appreciable they said .In addition to this, vital comments & suggestions had been given; followed this closing ceremony and certificate program took part

አሶሳ ዩኒቨርሲቲለነባር ቦርድ አመራር  የሽኝትና ለአድሱ አመራር የቅበላ ፕሮግራም አደረገ፤

 

የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ግንቦት 18/2011 ዓ/ም የዩኒቨርስቲው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በተገኙበት ለነባር የቦርድ አመራር አባላት የሽኝትና ለአድሱ የአቀባበል ፕሮግራም አካሄደ፡፡ 

የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ሀይማኖት ዲሳሳ በፕሮግራም መክፈቻ ከነባር ቦርድ አባላት  መካከል  በሥራ ምክንያት ወደ ሌላ ቦታ የሚሄዱ መኖራቸውን አውስተው ፕሮግራሙ ነባር  አመራሮች ያላቸውን ልምድ ለአድስ የቦርድ አባላት የሚያካፍሉበትና የሥራ ትውውቅ ለማድረግ ይረዳል ብለዋል፡፡

የሽኝት ፕሮግራም የተደረገላቸው የቦርድ አመራሮች ዩኒቨርስቲው እንደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት ሊወጣ የሚችለው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ተናበው ሲሰሩ መሆኑን  ገልፀዋል፡፡ በመቀጠልም የቦርድ አመራር በሚቀርብለት ሪፖርት ተወስኖ የሚቀርብ ብቻ ሳይሆን ታች ድረስ ወርዶ ተጨባጭ ሁኔታዎችን ማረጋገጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ በተጨማሪም የዩኒቨርቲው ከፍተኛ አመራር ሁሉንም ሠራተኛ ቢያንስ በአመት ሁለት ግዜ በማወያየት ሥራዎችን በመገምገም የተሸለ አፈፃጸም ማስመዝገብ እንደሚቻል ምክረ-ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡ አያይዘውም በሄዱበት ቦታ ሁሉ ለአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አምባሳደር እንደሚሆኑ ቃል ገብተዋል፡፡

የአሶሳ ዩኒቨርስቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ከኮሌጁ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና ሰጠ፤

ግንቦት 14/2011 ዓ/ም በዩኒቨርስቲው ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ሥር ከሚገኙ የትምህርት ክሎች ውስጥ በትምህርት እርከኑ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ አስራ አራት ተማሪዎች የማበታቻ ሽልማት ተሰጧቸዋል፡፡ 

የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን  የሆኑት መ/ር አስማማው አባት በፕሮግራሙ መክፈቻ የማበረታቻ ሽልማቱ በተማሪዎች የትምህርት አቀባበል ላይ የፍክክር መንፈሰ በመፍጠር የተሳለጠ የመማር ማስተማር አውድ እንዲፈጠር ይረዳል ብለዋል፡፡ አያይዘውም የተለያዩ ማነቃቂያ ስልቶችን  በመጠቀም ተማሪዎቹን በእውቀት፣ በክህሎት እና በአመለካከት በመገንባት ራሳቸውን ብቁ በማድረግ ተወዳዳሪ ሆነው የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚችሉ አውስተው ፕሮግራሙ በየሴሚስተሩ ቀጣይነት እንደሚኖረውም ገልፀዋል፡፡

አሶሳ ዩኒቨርስቲ ለማረሚያ ቤት መምህርን ስልጠና  ሰጠ

የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርስቲው ጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ትምህርት ክፍል መምህራን ጋር በመተባበር ከሶስቱም ዞን ለተውጣጣ ለ45 መምህራን በተማሪ ተኮር መማር ማስተማር፣በተከታታይ ምዘና እና በመምህራን የሙያ ማሻሻያ ዙሪያ ከግንቦት 12/2011 ዓም ጀምሮ ተከታታይ አራት ቀናት ስልጠናው  ተሰጥቷል፡፡

የአሶሳ ዩንቨርስቲ ጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ትምህርት ክፍል መ/ር የሆኑት መ/ር ታደለ ተስፋዬ እና መ/ር ገመቹ መርጋ የስልጠናውን አስፈላጊነት አስመልክተው መ/ራን በሚያስተምሩት የትምህርት አይነት በይዘትም ሆነ በሥነ ዘዴ ራስን አብቅቶ፣ በመማር ማስተማር ሂደቱ የሚታዩ ችግሮች በሰከነ መልኩ እንዲፈቱ የመፍትሔው አካል በመሆን የትምህርት ጥራትና አግባብነትን የማረጋገጥ ሥራ መሥራት እንደሚኖርባቸው ለማስታወስ ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ጥናትና ምርምር የማካሄድ እና የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግሮች በምርምር የመቅረፍና የማስተማር ኃላፊነት እንደአለባቸው ገልጸዋል፡፡  አያይዘውም ሰልጣኞቹ ከሥልጠናው በኋላ የሚገኘውን ግንዛቤ በየትምህርት ቤታቸው ላሉ መምህርን ማካፈል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በመተከል ዞን ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ፤

ከዩኒቨርስቲው የማኔጅመንትና የካውንስል አባላት የተውጣጣ ቡድን ሚያዚያ 19/2011 ዓ.ም በመተከል ዞንና አጎራባች በሆነው ጃዊ ወረደ ተከስቶ በነበረው ግጭት ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ግንቦት 11/2011 ዓ.ም ግምታቸው 241650 ብር የሚሆኑ የምግብ ዱቄትና የቤት መገልገያ ቁሳቁሶች  በመያዝ የተፈናቃዮቹን የኑሮ ሁኔታ ተዘዋውሮ በመመልከት ጭምር ነዉ ድጋፉን ያደረገው፡፡ የአመራር ቡድኑ ተዘዋዉሮ የተመለከተዉ  በፓዌ ወረዳ በአልሙ ቀበሌ እና በግልገል በለስ ሁለተኛ ደረጃ ትም/ት ቤት ተጠልለዉ የሚገኙ ወገኞችን ነዉ፡፡   

      

 

የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች ያሉበትን ሁኔታ ከተመለከቱ  በኋላ በድርጊቱ እጅጉን ማዘናቸዉን ገልፀዋል፡፡  አያይዘዉም   በቦታዉ የተገኘዉ  የዩኒቨርሲቲዉ አመራርና ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች የተውጣጣው ቡድን በቀጣይ የተፈናቃይ ወገኖችን ችግር በዘላቂ ሁኔታ ለመፍታት ምን መሰራት እንዳለበት ለማጥናትና ለመለየት እንደሆነ ከፍተኛ አመራሩ አብራርቷል፡፡

ተፈናቃይ ወገኖች በበኩላቸው አሶሳ ዩኒቨርስቲ ካደረገላቸው ድጋፍ በበለጠ የተፈናቃዮቹን የኑሮ ሁኔታ ለማየት ቡድን አቋቁሞ በቦታው በመገኘቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳ ተፈናቃዮቹ ግጭቱ ከመከሰቱ በፊት ለዘመናት በመቻቻል፣ በመደጋገፍ፣ በአብሮነት የጋራ እሴት በመገንባት ሲኖሩ እንደነበር አስታዉሰው በአሁኑ ሰዓት የተፈጠረው ግጭት ከላይ እስከ ታች ባለዉ የመንግስት አደረጃጀት አስቸኳይ መፍትሄ ተሰጥቶት ወደ መኖሪያ ቀያቸው 

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ጉዳይና ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል ዳይሬክቶሬት ለተማሪዎች እና ሠራተኞች ስለ አደንዛዥ ዕጽ ጎጂነት ስልጠና ሰጠ

 

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ጉዳይና ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል ዳይሬክቶሬት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ልማት ማህበር፣ የአሶሳ አካባቢ ጥበቃ ማህበር እና ተስፋ ሰጪ ኤች አይ ቪ በደማቸው ያለ በጎ አድራጎት ማህበር ጋር በመተባበር በጫትና ተያያዥነት ያላቸው አደንዛዥ ዕጾች ዙሪያ ለተማሪዎችና አስተዳደር ሰራተኞች ከሚያዚያ 11-12/2011 ዓ.ም ተከታታይ ለሁለት ቀናት ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በሥልጠናው መክፈቻ ላይ የአሶሳ አከባቢ ጥበቃ ማህበር ኤስክየቲቭ ዳይሬክቴር አቶ መንግሥቱ ባየታ ተገኝቶ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ ዳይሬክተሩ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት ሰልጣኞች ከስልጠናዉ መልስ በሚሄዱበትም ሆነ በዩኒቨርሲቲዉ ቆይታቸው ለአካባቢው ማህበረሰብ፣ ለጓደኞቻቸው እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸዉ ስለ አደንዛዥ ዕጽ የሚያስከትለዉ ችግሮች ዙሪያ በማስተማርና ግንዛቤ በመፍጠር ሀላፊነታቸውን እንድወጡ አሳስቧል፡፡ የስልጠናዉ ዓላማም ትዉልድ የማዳን ሥራ እንደመሆኑ ሠልጣኞች ትኩረት ሰጥቶ መከታተል እንዳለባቸዉ ተናግረዋል፡፡

በሥልጠናዉም ጫትና ተያያዥነት ያላቸዉ አደንዛዥ ዕጾች፣ የሕይወት ክህሎት እና የስሜት ብልህነት ዋና ርዕሶች ሲሆን በያንዳንዱ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሰፊ ገለጻዎችና ዉይይቶች ተደርጎባቸዋል፡፡  

 

በስልጠናው ላይም አንዳንድ ሰልጣኞች እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲዉ በአደንዛዥ ዕጽ ዙሪያ ያዘጋጀዉ ስልጠና እጅግ ጠቃሚ መሆኑን በመግለጽ በጉዳዩ ላይ ወደ ፊትም በቀጣይነት ሥልጠናዎችን ለተማሪዎችና ለሚመለከተዉ ሠራተኞች መሥጠት እንዳለበት አስተያዬታቸዉን ሰጥተዋል፡፡ አክለዉም በዩኒቨርሲቲዉ ግቢ ዉስጥ የሚገኙ ንግድ ቤቶች ሲጋራና ጫት  እንዳይገባ በየጊዜው ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ የግንዛቤ ማስጨበጫዉ ከዩኒቨርሲቲዉ ዉጭም ለአሶሳ ከተማ ማህበረሰብ በስፋት መሰጠት እንደሚያስፈልግ ሀሳባቸዉን ሰጥተዋል፡፡

                  ማሳሰቢያ ለአሶሳዩኒቨርሲቲተማሪዎች በሙሉ፤

እንደሚታወቀዉ በመንግሥት ተቋማት ዉስጥ የማንኛዉንም የሀይማኖትና የፖለቲካ ድርጅት መልዕክት ያለበት T-Shirtሆነ አርማ ይዞ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ ነዉ፡፡ ይሁንና በዩኒቨርሲቲያችን ሚያዚያ13/2011 ዓ.ም በቁጥር60 የሚሆኑተማሪዎች የአንድን የፖለቲካ ፓርቲ ጽሑፍ ያለበትT-Shirt ለብሠው በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል።ይህ ደግሞ ሳይማር ወደ ዮኒቨርሲቲ የላከውን ወላጅ አደራ የመማር፣የመመራመርና የማህበረሰብ አገለግሎት ተልዕኮን ወደ ጎን በመተው ከመጣበት አጀንዳ ውጭ ለሆነ ጉዳይ ዉድ ጊዜውን እያባከነ መሆኑ በእጅጉ መታረም ያለበት ድርጊት መሆኑን በጥብቅ እናስገነዝባለን::

 ከዚህ ጋር ተያይዞም በድርጊቱ ውሰጥ የተሳተፉ ተማሪዎች በፀጥታ ሀይል እንደታሰሩ ተደርጎ በማህበራዊ ሚድያ የሚናፈሰዉ ወሬ ፍፁም የተሳሳተ መረጃ እንደሆነና የፖለቲካ መልዕክት የያዘ T-Shirt ለብሰዉ የተገኙ ተማሪዎች በአሁኑ ሰዓት በትምህርት ገበታቸው ላይ መሆናቸውን እናሳዉቃለን፡፡ በቀጣይም በዪቨርሲቲው ህግ እና ደንብ መሠረት ጉዳዩን አጣርተን የማሰተካከያ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን አውቃችሁ ሰለማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ከአደራ ጭምር እናሳስባለን::

አሶሳ  ዩኒቨርሲቲ  የእጩ  ፕሬዝዳንት  መልማይና  አስመራጭ  ኮሚቴ  እስከአሁን  ባከናወናቸው  ተግባራት  ዙሪያ  መግለጫ  ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው የፕሬዝዳንት መልማይና አስመራጭ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኡመር አህመድና ሌሎች የኮሚቴዉ አባላት ሚያዚያ 10/2011 ዓ.ም ኮሚቴው ባከናወናቸው ተግባራት ዙሪያ ለዩኒቨርሲቲው ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ኮሚቴው በመግለጫው የእጩ ፕሬዝዳንት መልማይና አስመራጭ ኮሚቴ በዩኒቨርሲቲው የተፈጠረውን የከፍተኛ አመራር ክፍተት ለመሙላት ተቋቁሞ ስራውን መጀመሩን አስታውሷል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዞ ኮሚቴው ከተቋቋመበት ቀን ጀምሮ ልምዶችን ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ቀስሞ በመመለስ የተሰጠውን ሀላፊነት ለመወጣት በመስራት ላይ እንደሆነ አስገንዝቧል፡፡

እስካሁን ከሰራቸው ስራዎች መካከልም  ኮሚቴዉ ሲገለጽ መጋቢት 19/2011 ዓ.ም በወጣው አድስ ዘመንና  Ethiopia Herlad ጋዜጣዎች የመወዳደሪያ መስፈርቱ ታትሞ እንዲወጣ ማድረግና ከመጋቢት 20/2011 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በEBC(በኢትዪጲያ ቴሌቪዥን) ከማታው 2፡00 ሰዓት ዜና በኋላ እንዲለቀቅ አስደርጓል፡፡ ከዚህ በመቀጠል  ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት መስፈርቱ ለሚያሟሉ አመልካቾች የምዝገባው ሂደት ሚስጥራዊነቱ በጠበቀ መልኩ እስከ ሚያዚያ 09/2011 ዓ.ም አከናውኖ ምዝገባውን ማጠናቀቁን አሳዉቋል ፡፡ በምዝገባ ሂደቱም ስድስት እጩ ተወዳዳሪዎች የተመዘገቡ  መሆናቸውን ኮሚቴው ገልዷል፡፡ በቀጣይ ጊዜያትም  የምልመላና የመረጣ ሥራዎችን የሚያደርግ እንደሆነ  ኮሚቴዉ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል፡፡ዩኒቨርስቲው የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈፃፀም  ሪፖርት ግምገማ አካሄደ

አሶሳ ዩኒቨርስቲ   የዘጠኝ ወር የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት  ሁሉም የተቋሙ የካውንስል አባላት በተገኙበት ሚያዚያ 09/2011 ዓ/ም ግምገማ አካሂዷል፡፡

ሪፖርቱን ያቀረቡት የዩኒቨርስቲው የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን አሰፋ ናቸው፡፡ ሪፖርት አቅራቢው እንደገለጹት ዩኒቨርስቲው በ2011 የትምህርት ዘመን በሰባት ኮሌጆች እና  በሶስት ትምህርት ቤቶች በአጠቃላይ 7,542 መደበኛ ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማር ሥራውን እያከናወነ  ይገኛል ብለዋል፡፡

በሪፖርቱም የ2011 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት የቁልፍ ተግባራት ዕቅድ አፈፃፀም እና የዓብይ ተግባራት እቅድ አፈፃፀም  ለካውንስል  አባላቱ ቀርቧል፡፡ የዘጠኝ ወራት ዓብይ ተግባራትና የቁልፍ ተግባራት የዕቅድ ክንውን  ለተግባራቱ የተሰጠ ክብዴት ከ100% ሲሆን አፈፃፀሙም በመቶኛ 76.33 ላይ መሆኑን ያመላክታል፡፡ ሪፖርቱም ለቤቱ ከቀረበ በኋላ ቤቱ የቀረበውን ሪፖርት  በጥልቀት ገምግሟል፡፡

በሪፖርቱም በጠንካራ ጎን የተነሱት ተግባራት ለመማር ማሰተማሩ ሥራ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩ፣ አዲስ ለተቀጠሩ መምህራን የሥራ ትውውቅ ሥልጠና መውሰዳቸው፣ የተለያዩ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች መሰራታቸው፣ የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው ሴት ተማሪዎች ድጋፍ መደረጉ በአብነት የሚጠቀሱ ናቸዉ፡፡

 

 ካውንስሉ ለቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት የሚገባቸው ጉዳዮች በዝርዝር አስቀምጠዋል፡፡ እንደአብነትም  በሪፖርቱ ላይ የግብዓት አቅርቦት አፈፃፀም በመቶኛ 100% ተብሎ የተቀመጠው የተጋነነ በመሆኑ መታየት እንዳለበት፣ በግብርናና ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ውስጥ የሚገኙ የአቢጋር፣ የሆሊሲቲ እና የጀርሲ የቀንድ ከብት ወደ ፋርሙ በማስገባት ሥራ የተጀመረ ቢሆንም  በየደረጃው ያሉ አመራሮች ዘርፉ ትኩረት አለመስጠት፣በግቢው ውስጥ እየተገነባ ያለው የቆሻሻ ማከሚያ ፕሮጀክት ግንባታ ሥራ በተያዘለት ግዜ ያለመጠናቀቅ እና በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት በመረጃ ተደግፈው ለአካባቢው ማህበረሰብ ተደራሽ አለመሆን የሚሉት ገዳዮች በዋናነት የተነሱ ናቸው፡፡    

 አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባለሙያዎች የBSC ስልጠና ሰጠ

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከህዝብ አስተዳደር ልማት አመራር ትምህርት ክፍል ጋር በመተባበር ለአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባለሙያዎች በሚዛናዊ ዉጤት ተኮር ሥርዓት (BSC) ዙሪያ ከሚያዚያ 01-05/ 2011 ዓ.ም በባምባሲ ከተማ ስልጠና ሰጥቷል፡፡የስልጠናዉ ዓላማ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባለሙያዎች ዘንድ ስለ ሚዛናዊ ዉጤት ተኮር ሥርዓት አተገባበር ዙሪያ ያለዉን የግንዛቤ ክፍተቶች ለመሙላት መሆኑን በስልጠናዉ መክፈቻ ላይ ተገልጿል፡፡

ሚዛናዊ ዉጤት ተኮር ሥርዓት (BSC) የተቀናጀ የስትራቴጂያዊ እቅድ ሥራ አመራር፣ ኮሚኒኬሽን እና የመለኪያ ሥርዓትን አጣምሮ የያዘ የለዉጥ መሣሪያ መሆኑን አሰልጣኞቹ አብራርተዋል፡፡ እንደ አሰልጣኞቹ ገለፃ BSC ስልታዊ እቅድ ሲሆን ስትራቴጂን ተግባራዊ ሊሆኑ ወደሚችሉበት ስትራቴጂያዊ ግቦች ለመመንዘር የሚያስችል ነዉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም BSC የፈፃሚዎችን የዕለት ተዕለት የሥራ ክንዉን ከተቋም ራዕይና ስትራቴጂ ጋር ለማስተሳሰር የሚያስችልና ዉጤትን የምንመዝንበት መሆኑን በሥልጠናዉ ተዳሷል፡፡ ጥቅሙም ተቋማዊ ተልዕኮን ለመፈፀምና መሳካቱንም ለመመዘን፣ ግልፅ የሆነ ተቋማዊ ራዕይና ስትራቴጂን ለመቅረጽ፣ ሁሉም ፈጻሚዎች የተቋሙ የወደፊት ስትራቴጂዎች፣ አካሄዶችና ድክመቶችን እንዲለዩና እንዲወያዩ መንገድ እንደሚከፍትም ተነስቷል፡፡ ሚዛናዊ ዉጤት ተኮር ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ የአንድን ተቋም ዉስጣዊና ዉጫዊ ግንኙነቶችን የበለጠ እንደሚያዳብርና ተቋማዊ አፈፃፀሞች በስትራቴጂ እንዲመራ ሁሉን አቀፍ እይታዎች ለመምራት ጥቅም እንዳለዉም ተጠቅሷል፡፡ በአጠቃላይ ሚዛናዊ ወጤት ተኮር ሥርዓት በሠራተኞች ዘንድ የባለቤትነትና ተጠያቂነት ስሜትና ቁርጠኝነት እንደሚፈጥር አስልጣኞቹ በስፋት አንስተዉ በትግበራ ወቅት ወደ ስህተት የሚወስዱንና ጥንቃቄ የሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ገላፃ ተሰጥቶበታል፡፡

ሚዛናዊ ዉጤት ተኮር ሥርዓት አመራር ወደ ትግበራ ለመቀየር የመጀመሪያዉ የለዉጡ አስቸኳይነት እና አንገብጋቢነት ግንዛቤ መፍጠር ወሳኝ መሆኑን በስልጠናዉ ተነስቷል፡፡ ለዚህ ስኬት መድረስ የበላይ አመራሩ ሥርዓቱን በባለቤትነት እና ቀጣይነት ባለዉ ሁኔታ መምራት እንደሚያስፈልግና ሥርዓቱ የአንድ ጊዜ ሳይሆን የሁል ጊዜ ሥራ አድርጎ መያዝ ያስፈልጋልም ተብሏል፡፡

በሥልጠናዉ የሚዛናዊ ዉጤት ተኮር ሥርዓት (BSC) ግንባታ ደረጃዎች ላይ ሰፊ ገለፃዎችና ዉይይቶች ተደርገዋል፡፡ ሥልጠናዉ በተግባር ልምምድ የታገዘ በመሆኑ ሠልጣኞቹ በእያንዳንዱ የBSC ግንባታ ደረጃ ላይ ጥልቅ ግንዛቤ መጨበጣቸዉን ተናግረዋል፡፡ አክለዉም አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለክልሉ እያበረከተ ያለዉ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች ጥሩ መሆኑንና ወደ ፊትም ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንዳለበት አስተያዬታቸዉን ሰጥተዋል፡፡ 

                                                የአሶሳ ዩኒቨርስቲ የግቢ ፅዳት ዘመቻ አካሄደ፤

 

በሀገር አቀፍ ደረጃ “ፅዱ አካባቢ ለትምህርት ጥራት” በሚል መሪ ቃል አካባቢያችንን በማፅዳት እንዲከበር ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተላለፈው መልዕክት መሰረት ዩኒቨርስቲው ሁሉንም የግቢውን ተማሪዎች፣ የአስተዳደር ሠራተኞች እና መምህራን እንዲሁም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት አከባቢ ጥበቃ ቢሮን በማሳተፍ የግቢ ፅዳት ዘመቻ በቀን 04/08/2011 አካሂዷል፡፡

ከጽዳት ዘመቻው በኋላ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ተወካይ ዶክተር ሀይማኖት ዲሳሳ ጽዱ አከባቢን መፍጠር ለመማር ማስተማር ሂደቱ መሳለጥ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ገልፀው ውስጣችንንም ከመጥፎ አስተሳሰብ፣ ከጥላቻና ከዘረኝነት በማጽዳት የሀገራችንን ሠላም በማረጋገጥ የበኩላችንን ሚና መወጣት ይኖርብና ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ አያይዘውም በጽዳት ዘመቻው ለተሳተፉ ባለድርሻ አካላት ሁሉ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

                       የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሠላም ምሽት አካሄዱ

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሠላም ፎረም አባላትና ተማሪዎች መጋቢት 07/ 2011 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲዉ የሠላም ምሽት አክብረዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ዓላማዉም  በዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች መካከል የቀዘቀዘ ግንኙነት ቀድሞ ወደ ነበረበት ፍጹም የሆነ ሠላማዊ አብሮ የመኖር ባህል ለመመለስ ታስቦ ነዉ፡፡

ፕሮግራሙ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የዩኒቨርሲቲዉ ተወካይ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ይማኖት ዲሳሳ እንደ ተናገሩት ተማሪዎች የራሳቸዉን ችግር በራሳቸዉ በመነጋገርና በመደማመጥ ችግሮቹን ከሥር መሠረቱ ለመፍታት ያደረጉትን እንቅስቃሴ እጅግ የሚያኮራ ተግባር መሆኑን አንስቷል፡፡ የዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች ወደዚህ ዩኒቨርሲቲ ተመድባችሁ የመጣቹበት ዓላማ ለመማር፣ ለመመራመርና ማህበረሰብ አገልግሎት ለመስጠት ነዉ ያሉት ዶ/ር ሀይማኖት ዲሳሳ ልዩነቶቻችን ዉቤታችን መሆኑን ከልብ በማመን የመከባበር ባህላችንን በመላበስ ዓላማችሁን አሳክታችሁለሀገራችን ህዳሴ የበኩላችዉን አስተዋጽኦ ማበርከት አለባችሁ ብለዋል፡፡ 

በሰላም ምሽቱ ፕሮግራም ላይ ኢትዮጵያዊነት ገኖ የወጣበት ሲሆን በወቅታዊ የሀገርቱ ሁኔታዎችን መሠረት በማድረግ የተለያዩ ድራማዎች፣ መነባነብና ግጥሞች በዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎቹ ቀርበዉ ለግንዛቤ ዉሏል፡፡

Assosa University Female Affairs and HIV/AIDS Prevention  Directorate Provide Research Training for Female Instructors

Assosa University Female Affairs and HIV/AIDS Prevention Directorate in collaboration with Research Directorate providedtraining for female instructors on research proposal writing fromMarch 11-14/ 2019.

The training was given by highly qualified professional in the field of research areas from Addis Ababa University, prof. Yalemtsehay Mekonen. Accordingly, the trainees had covered topics related to proposals development in their staying while taking the training.  As the training was more practical aspect, a lot of experiences were shared among the trainer and the trainees. Finally, the trainees developed proposal in their respective groups based on their colleges and presented it to the all training participants.

                                አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የፀረ-አደንዛዥ ክበብ አቋቋመ

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ጉዳይና ኤች.አይቪ.ኤድስ መከላከል ዳይሬክቶሬት ከአሶሳ አካባቢ ጥበቃ ማህበር ጋር በመቀናጀት በአደንዥ ዕጽ ዙሪያ መጋቢት 05/2011 ዓ.ም ከዩኒቨርሲቱዉ አመራርና ተማሪዎች ጋር ዉይይት አድርጓል፡፡ዉይይቱን የከፈቱት የዩኒቨርሲቲዉ የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ትምህርት ቤት ዲን መ/ር ጠቅል አላማዉ እንደ ተናገሩት በአደንዛዥ ዕጽ ተጎጂ የሆኑ ማህበረሰቦችን መታደግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፆ የችግሩ ተጋላችጭ የሆኑት ወጣቶች እንደመሆናቸዉ ከማስተማር በተጨማሪ ክበብ በማቋቋም በችግሩ ላይ መረባረብ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ጥናታዊ ጽሑፎች የቀረቡ ሲሆን የአደንዛዥ ዕጽ በሀገራችን ወጣቶች በተለይም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በይበልጥ የችግሩ ተጠቂዎች መሆናቸዉን ጥናቶች እንደሚያረጋግጡ ተነስቷል፡፡ በቀጣይም ይህንን አስከፊ ችግር ለመከላከል እና ለመቀነስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጂት መስራት እንዳለባቸው በውይይቱ ላይ ትኩረት ተሰጥቶበታል፡፡ “አደንዛዥ ዕጽ እና ማህበራዊ ተጽዕኖዎች” በሚል ርዕስ መ/ር ዜናው ዓለም ያቀረቡት  ጽሑፍ አደንዛዥ ዕጽ ማህበረሰቡን እየጎዳ እንደሆነ በተለይም ደግሞ ወጣቱን አምራች ኃይል በሱስ ተጠምዶ እንዲውል እና የእለት ከዕለት ተግባሩን በጥሞና እንዳያከናውን አሉታዊ ተጽዕኖ እያስከተለ ይገኛል ብሏል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የአደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚዎች ከፍተኛ የሆነ የጤና እና የማህበራዊ ቀውስ እንደሚያስከትልባቸዉ የተገለጸ ሲሆን በዓለም ላይ በሱስ የተጠቁ ሰባት ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች እንዳሉና ከዚህ መካከል አንድ-አራተኛዉ ሕይታቸው እንደሚያልፍ ተገልጸዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ግጥምና ትምህርታዊ ጭዉዉት በዙምባራ ህፃናትና ወጣቶች የኪነ-ጥበብ ቡድን ቀርበዉ ለግንዛቤ ማስጨበጫ ዉሏል፡፡ በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲዉ የፀረ-አደንዛዥ እጽ ክበብ ማህበር መተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ ሰነድ በክበቡ መስራች ኮሚቴ የቀረበ ሲሆን እረቂቅ ሰነዱን ገምግሞ በማጽደቅ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መርጧል፡፡ 

 

                            አሶሳ ዩኒቨርሲቲ 43ኛዉን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓል በድምቀት አከበረ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ108ኛ በሀገራችን ለ43ኛ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲያችን ደረጃ ደግሞ ለ8ኛ ጊዜ ‹‹የላቀ ትኩረትና ቁርጠኝነት ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት›› በሚል መሪ ቃል በዩኒቨርሲቲዉ የካቲት 29/2011ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡

          የቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ነፊሳ አልማሃዲ በመክፈቻ ንግግራቸዉ እንደተናገሩት ሀገራችን መካከለኛ ገቢ ካላቸዉ ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ እያደረገችዉ ባለዉ የለዉጥ እንቅስቃሴዎች መካከል አንዱ ሴቶችን በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካ ተሳትፎ ተጠቃሚነት ላይ በ2ኛዉ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዉስጥ ከምን ጊዜዉም የበለጠ አስደማሚ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ እንደ አብነትም ያነሱት ከዚህ በፊት በወንዶች ብቻ ተሸፍነዉ የነበሩ የሹመት መዋቅሮች 50% በሴቶች እንዲሸፈኑ ተደርገዋል ብለዋል፡፡ አሶሳ ዩኒቨርሲቲም ካሉት ሰባት የሥራ አመራር ቦርድ ሦስቱ በሴቶች እንዲሸፈኑ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡

 

ወ/ሮ ነፊሳ አልማሃዲ አያይዘዉም የበዓሉ ዓላማ የዓለም መንግስታት የሴቶች ጉዳይ የልማት ፣የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ጉዳይ እንደሆነ አምነዉ በመቀበል ፖሊሲዎቻቸዉን፣ ህጎቻቸዉንና አሰራሮቻቸዉን በመፈተሸ ሴቶች ላይ የሚፈፀሙ መድሎዎችን እንዲያስወግዱ እና የሴቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን እንዲያረጋግጡ ማነሳሳት ነዉ ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ የአለም ክፍሎች ያሉ ሴቶች የሚደርስባቸዉን ጭቆናና የመብት ጥሰት የሚያወግዙበት፤ አንድነታቸዉን በማጠናከር ድምጻቸዉን በጋራ የሚያሰሙበት እንዲሁም ልምድ የሚለዋወጡበትና ለበለጠ ትግል ተቀናጅተዉ በመንቀሳቀስ ቃል የሚገባበት ቀን መሆኑን በመጠቆም መርሀ-ግብሩን በይፋ ከፍተዋል፡፡

 

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሴቶችና ህፃናት ቢሮ ሓላፊ ወ/ሮ ሃጂራ ኢብራሂም በበኩሏ በሀገርቱም ሆነ በክልላችን ዉስጥ የሚካሄድ የህዝብን ተሳትፎ የሚመለከት ማናቸዉም እንቅስቃሴ የህብረተሰቡ ግማሽ አካል የሆኑ ሴቶቻችን ግምት ዉስጥ ሊስገባ ይገባል ብሏል፡፡ አክለዉም ሴቶችን ያላሳተፈና ተጠቃሚ የማይሆኑበት ማንኛዉም ዓይነት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ የተፈለገዉን የልማት ዉጤት ማሳካት እንደማይችል ገልፀዋል፡፡ ሴት ልጆችን ለምርምር፣ ለፈጠራና ለመሪነት ማብቃት የወቅቱ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም መንግሥት ይህን ከግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት ሴቶችን አስመልክቶ በፌዴራልም ሆነ በክልል ደረጃ የተለያዩ ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች የተቀረፁ መሆኑን ግልፀዉ አፈፃፀሙን ሙሉ በሙሉ ሁሉንም የማህበረሰብ አካላት ያረካ ባይሆንም ተግባራዊ እየተደረገ እንደ ሆነ በንግግራቸዉ አንስተዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የተለያዩ ትይንቶች በዙምባራ ህጻናትና ወጣቶች ክነ-ጥበብ ቡድን ቀርበዉ ለግንዛቤ ማስጨበጫ ዉሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በዓሉን ምክኒያት በማድረግ የዉይይት መነሻ ጽሑፍ ቀርበዉ ሰፊ ዉይይት ተካሂደዉበታል፡፡ በመጨረሻም የደም ልገሳ ፕሮግራም በማካሄድ ክብረ በዓሉ ተጠናቋል፡፡

 

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ካለዉ እድሜ በክልሉና ከአጎራባች ክልሎች ከሚገኙ ተቋማት ጋር ዉጤታማ የሆነ ሥራ ሠርቷል ማለት ባይቻልም ቅድሚያ መካሄድ ያለባቸዉን ሂዴቶችን በማለፍ አመርቂ ሥራዎችን ለመሥራት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

የዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች በጣና በለስ የተቀናጀ የሥኳር ልማት ፕሮጀክት ተቋም የሚሰሩ ሥራዎችን በጥልቀት ተዘዋዉረዉ ከጎበኙ በኋላ ከፕሮጀክቱ አመራሮች ጋር ዉጤታማ የሆነ ዉይይት አካሂደዋል፡፡ የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ ሁሉንም የሳይንስ መስኮች አካቶ በመሥራት ላይ ያለ በመሆኑ ለዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች የተግባር ልምምድ ለማድረጊያና ከምረቃ በኋላ የሥራ ዕድል በመፍጠር መተኪያ የሌለዉ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት መረዳት ተችሏል፡፡ የስኳር ፕሮጀክቱ 75 ሺ ሄክታር  ማሳ  ለሸንኮራ አገዳ ማልሚያ እርሻ አዘጋጅቷል፡፡ 130 ሺዉን ሄክታር አልምቶታል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎንም እንስሳት ማድለብ፣ የአትክልትና ፍራ ፍሬ ልማት በመስኖ ያለማል፡፡ የፋብሪካዉ ግንባታም ከጥቅት ወራት በኋላ ተጠናቆ ወደ ስኳር ማምረት ሥራ ይገባል፡፡ እንግዲህ ፋብሪካዉ ይህን ሥራ በሚያከናወንበት ጊዜ ወደ 35 ሺ የሚጠጋ የሰዉ ሀይል ያስፈልጋል ነዉ የተባለዉ፡፡ ለዚህም ነዉ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከተቋሙ ጋር ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረመዉ፡፡ 

 

ዩኒቨርሲቲዉ በሚሰራቸዉ የምርምር ሥራዎች በበኩሉ በአትክልትና ፍራፍሬ በሽታዎች ለምሳሌ በማንጎ በሽታ ላይ እና በእንስሳት በሽታ ዙሪያ ዉጤታማ የሆነ ምርምር በማድረግ በቅንጅት ከስኳር ልማት ፕሮጀክቱ ጋር እንደሚሰራ ነዉ የተገለፀዉ፡፡ ዩኒቨርሲቲዉ ይህ የስኳር ልማት ፕሮጀክት በአከባቢዉ መኖሩ ጋር ተያይዞ የሚከፍታቸዉን ፕሮግራሞች በድግሪ መርሃ ግብር የኦሪቲካልቸርና የመስኖ ምህንድስና ትምህርት ክፍሎችን ከፍቶ ቢያስተምር መተባበር እንደሚቻል ተጠቁሟል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ የዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች በፓዌ አጠቃላይ ሆስፒታል በመገኘት ግልፅ የሆነ ዉይይት አድርገዉ ከዚህ በፊት የዩኒቨርሲቲዉ የህክምና ሳይንስ ተማሪዎች ለተግባር ልምምድ በሚወጡበት ጊዜ ሲያጋጥሙ የነበሩ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ምክክር አድርገዋል፡፡ ሆስፒታሉም እዉነተኛ የዩኒቨርሲቲዉ አጋር በመሆን ለተማሪዎቹ የተግባር መማሪያ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ዩኒቨርሲቲዉ በበኩሉ የሆስፕታሉን ሠራተኞች የትምህርት ደረጃቸዉን ለሚያሻሽሉ በድግሪ ፕሮግራም ትብብር ሲያደርግ ቆይቷል፤ ለወደፊትም እንደሚቀጥልበት አሳዉቋል፡፡ ለነዚህ መሰል ተግባራት በጋር ለመሥራት ነዉ ሁለቱ ተቋማት የዉል ስምምነት የተፈራረሙት፡፡ 

 

ከዚህ በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲዉ ከግልገል በለስ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ ጋር በቅርብ ጊዜ የመግባቢያ ሰነድ ለመፈራረም ያስችል ዘንድ በጋራ የሚሰሯቸዉን ሥራዎች በዉይይት ለይቷል፡፡ ከነዚህም ጥቂቶቹ ሁለቱም ተቋማት የማስተማር ሥራ የሚሰሩ በመሆናቸዉ ዩኒቨርሲቲዉ በ2011 ዓ.ም ክረምት ጀምሮ በሦስት የነባር ብሔረሰብ ቋንቋዎች የድግሪ መርሃ ግብር የሚሰጥ ሲሆን ኮሌጁ ደግሞ በድፕሎማ መርሃ ግብር ሲያስተምር የቆየ በመሆኑ ያሉትን የማስተማሪያ ሞጁሎችንና መምህራንን ዩኒቨርሲቲዉ የሚጠቀምበት ሂደት ለማመቻቸት ታስቧል፡፡ በአንጻሩም ለኮሌጁ መምህራን የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎች መስጠት፣ የቤተ ሙከራ ቁሳቁሶችንና የመማሪያ መጽሐፍትን ዩኒቨርሲቲዉ እገዛ የሚያደርግ መሆኑ ተለይቷል፡፡ ኮሌጁ ከዚህ በፊት የዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች ለተግባር ትምህርት ወደ ሌሎች ቦታዎች ሲሄዱ የመኝታ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ የአጋርነት ሚናዉን ሲያደርግ የነበረ ነዉ፡፡ የፓዌ የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤትንም ዩኒቨርሲቲዉ ድጋፍ የሚያደርግባቸዉን መስኮች ለይቷል፡፡ በፓዌ ግብርና ምርምር ግቢ በመገኘትም  ትምህርታዊ ጉብኝት አድርጓል፡፡ 

 

በተመሳሳይ መልኩ የዩኒቨርሲቲዉ አመራር በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ከዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያይቶ በጋራ የሚሰሩባቸዉን ነጥቦች በዝርዝር ለይቷል፡፡ ከነዚህ መካከል በጥቂቱ በአከባቢ ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ በዘመናዊ ግብርና፣ በህዳሴዉ ግድብ ዙሪያና በቱሪዚም ሀብት ልማት ዘርፎች ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር አብሮ በመስራት ሁለቱም ተቋማት ዉጤታማ መሆን እንደሚችሉ በዉይይቱ ተገልጿል፡፡ ከዚህም አልፎ በአማራ ክልል ካሉ ሰባት የኒቨርሲቲዎች የጋራ ፎረም ያቋቋሙ በመሆናቸዉ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከነዚህ ዩኒቨርሰቲዎች በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ስምንተኛ የፎረሙ አባል ሆኖ ቢቀላቀል በጋራ ለመስራት የሚያስችል መልካም አጋጣሚ እንደሆነ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በኩል ተገልጿል፡፡ 

 

Establishment of Tropical and Infectious Disease Research Center at Assosa University

The university Research Directorate organized work shop program on February 9, 2019 so as to get an input from different stakeholders to Establish Tropical and Infectious Disease Research Center.

On this workshop prof.Delnesaw Yewalaw:from Jimma University,Prof.Gobena Amen:from Addis Ababa University,Dr.Takele Tekelu:from University of Gonder, and regional health experts were  participated.

The opening Speech of the program was addressed by the university delegate President Dr. Haimanot Disassa. The Delegate president on his opening remark "the research center which is established at ASU will enrich multidisciplinary activities and it will solve societal problems in the region "he said. Dr.Desta Ejeta: Tropical and Infectious Disease Research Center coordinator, on his part presented the fundamental objective of Research Center and what it will study. As Dr.Desta  mentioned" the tropical diseases that are prevalent in or unique to tropical and subtropical regions .The disease such as malaria, dengue, schistosomiasis, African try ….and so on .As Assosa  is the hot spot of  these disease  this research  center  will play a significant role  in the area " he said.

Then after, the professionals in the field : prof.Delnesaw Yewalaw and Prof. Gobena Amen suggested that  as  Tropical and infectious Disease are many in numbers and  kinds .So ASU research Center should limit and specify the scope of the Research Center. They also recommended the members of scientific boards to be added in and out of the country and some ways to generate financial source for the effectiveness of the Research center. On the other hand, the regional experts also commented that, in order to establish the center and to make successful, collaborative work with the regional, national and international partners is preferable.

On the occasion, ASU mentioned the following four upcoming centers planned to be established. 

 

1. Agricultural technology Adaptation and Improve Prod activity.

2. Center for Environmental Management and Protection.

3. Center for Education Research and Partners Engagement.

4. Training and Resource center

As many scholars agreed it is obvious those Research Center will provide education and training in research and related skills, especially for graduate and under graduate students.  

 

 

ASSOSA UNIVERSITY APPROVED THE ESTABILISHED SEARCH AND SELLECTION COMMITTEE TO APPOINT PRESIDENT

Assosa University established the search and selection committee for the nomination of its president on 8th February, 2019.

According to Dr. Haimanot Disassa, vice president for Research and Community Service and the delegates of Assosa University, this committee was carefully selected to represent their group based on the directives of the Ministry of Science and Higher Education Institutions’ document. Here, the representatives of the University board, the senate, the teaching staff, the admin staff and the students were selected a head of the program by its own schedule. These representatives presented in front of the University senate to hand over the duties and to be a member of the search and selection committee legally. 

 

Finally, the University senate discussed on the profiles of the president selection criteria in detail and approved the committee members to officially start their duty. The committee members are Mr. Umer Ahmed from the University Board, Mr. Tekil Alamaw from the Senate, Mr. Jabir Hamza from the teaching staff, Mr. Takele Mekonnen from the admin staff and Mr. Minyahil Simachew representative of the students.  

 

የዩኒቨርሲቲዉ የሴቶች ጉዳይና  ኤች አይቪ ኤድስ መከላከል ዳይሬክቶሬት በሦስት ወረዳዎች ለሚገኙ ሴት ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ስልጠና ሰጠ፡፡

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ጉዳይና ኤች አይቪ ኤድስ መከላከል ዳይሬክቶሬት ከጥር 21-25/ 2011ዓ.ም ባለዉ ጊዜ በባምባሲ፣ በሆሞሻና በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ ሴት ተማሪዎች በቦታዉ በመገኘት የሕይወት ክህሎት ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠናው የተሳተፉ የ1ኛ ደረጃ፣ የ2ኛ ደረጃና መሰናዶ እንዲሁም ከ1ኛ እስከ 3ኛ ዓመት ለሚማሩ የኤም ኤ ኮሌጅ ተማሪዎች ሲሆን የስልጠናው ዋና ዓላማም ሴት ተማሪዎች ራሳቸውን በማብቃት ወደ ፊት በሕይወት ዘመናቸዉ የሚያጋጥሟቸውን ሁለንተናዊ ተግዳሮቶችን በቀላሉ ማለፍ እንዲችሉ ለማድረግ መሆኑ መገንዘብ ተችሏል፡፡ ይህም ሴት ተማሪዎች በራስ የመተማመን ክህሎት ኖሮአቸው ወደፊት እራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውን ብሎም ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን አሰልጣኞች ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ሴት ተማሪዎች በትምህርት ቤትም ሆነ በአካባቢያቸው ስለሚያጋጥማቸው ፆታዊ ትንኮሳ ለመከላከል እንዲሁም እራሳቸውን ከኤች አይቪ ኤድስ፣ ከአባለዘር በሽታና ካልተፈለገ እርግዝና እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው  በስልጠናው ተዳስሷል፡

በሥልጠናዉ ላይ ሠልጣኞች የራሳቸዉን ጠንካራና ደካማ ጎን  ማየት እንደ ቻሉ ተናግረዉ ወደ ፊትም ጥሩ ጎናቸዉን በማዳበርና ክፍተታቸዉን  ለመሙላት ግንዛቤ ያገኙበት እንደሆነ ሀሳባቸዉን ገልፀዋል፡፡ አክለዉም ስልጠናዉ ለወንዶችም አስፈላጊ መሆኑን አንስተዉ ዩኒቨርሲቲዉ በዘርፉ የሚሰጣቸዉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ላይ እነሱንም ቢያካትት ለበለጠ ግቡን እንደሚመታ ተናግረዋል፡፡  

                                                     

 Dear Assosa University students, this is to notify you that Basic and updated academic calendar of

2011 E.c for 2nd year and above Regular program has been summarized as follow.

 

 
 
 

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሥዕል አዉደ ርዕይ አካሄደ

ዩኒቨርሲቲዉ ከሰኔ 03-05/2009ዓ/ም በባንቡ ፓራዳይዝ ሆቴል ለ2ኛ ጊዜ ለእይታ ያቀረበዉ የሥዕል አዉደ ርዕይ የምረቃ በዓል ያደረገ ሲሆን ሥራዎቹ በፒካሶ የሥዕል አርት ክለብ በሰዓሊ ፋሲል ሙሉጌታ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ፈጠራና ባህል ማዕከል ዳይረክቶሬት ጋር በመተባበር የተሠሩ መሆኑን መገንዘብ ተችለዋል፡፡

የተሰሩት ሥዕሎች በከፊል
አዉደ ርዕዩን የከፈቱት የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሀይማኖት ዲሳሳ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲዉ እንደዚህ አይነት ልዩ ችሎታ ያላቸዉን ተማሪዎች ማጠናከርና እዉቅና መስጠት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዉ ወደ ፊትም ዩኒቨርሲቲዉ ከጎናቸዉ እንደሚቆም ቃል ገብተዋል፡፡ የተሠሩት የሥዕል ሥራዎቹም ጥሩና አበረታች መሆናቸዉን ጭምር ተናግረዋል፡፡

 

ሰዓሊዉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የመካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ ሲሆን ወደዚህ ሙያ የተቀላቀለዉ የ2ኛ ዓመት ተማሪ እያለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ተማሪዉ እስካሁን ለዚህ ሥራ በግሉ ከ ብር 10,000 በላይ እንዳወጣና ለኪነ-ጥበቡ እድገት የዩኒቨርሲቲዉ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡ ይህንን አኩሪ ሥራ ራሱ ባቋቋመዉ ‘’ፒካሶ የሥዕል አርት ክለብ’’ ከሥሩ 750 አባላት በላይ በማሰለፍ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተማሪዉ ጨምሮ ገልፀዋል፡፡ 

ተመልካቹ የሥዕል ሥራዎቹን ሲጎበኙ
አንዳንድ አስተያዬት ሰጪዎች በተማሪ ፋሲል ሙሉጌታ የተሰሩት የሥዕል ሥራዎችን አድንቀዉ ይበልጥ ለማጠናከር የዩኒቨርሲቲዉ ድጋፍ ወሳኝ መሁኑን ገልፀዉ ዩኒቨርሲቲዉ የአርት (ኪነ-ጥበብ) ትምህርት ቤት ቢከፈትላቸዉ ከዚህ የበለጠ መስራት እና ብዙ ተከታዮችን ማፍራት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

  

በአዉደ ርዕይዉ የተሳተፉት አስተያዬት ሲሰጡ