አሶሳ ዩኒቨርሲቲ  ከአስር የክልል ሴክተር  መስሪያቤቶች  ጋር  የጋራ የመግባቢያ ሰነድ  ተፈራረመ

ዩኒቨርሲቲው ሰኔ 15/2ዐዐ9 ዓ/ም ከክልሉ ሴክተር መስሪያቤቶች ጋር በጋራ ለመስራት እንዲችል የውል ስምምነት / Memorandum of understanding/ ተፈራርሟል፡፡

 

በበጀት ዓመቱ ጥሩ የስራ አፈፃፀም ስመዘገቡ ሰራተኞች እውቅና ተሰጠ

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በ22/11/ዐ9 ዓ.ም በ2ዐዐ9 የበጀት ዓመት ጥሩ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የአስተዳደር ሰራተኞች ፣ መምህራን ፣ የት/ት ክፍል ሀላፊዎች ፣ አስተባባሪዎች ፣ ቡድን መሪዎች እና መካከለኛ አመራሮች የምስክር ወረቀትና የገንዘብ ሽልማት አበረከተ፡፡

ያንብቡት…

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በክልሉ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የማጠናከሪያ ት/ት በመስጠት ላይይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሀምሌ ወር 2ዐዐ8 ዓ.ም በሶስቱም ዞኖች ለተውጣጡ በክልሉ የሚገኙ ተማሪዎችን ከክልል ት/ት ቢሮ ጋር በመሆን ምልመላውን ካደረገ በ|ላ ትምህርቱን በመስጠት ነበር ይህን የክረምት የመጠናከሪያ ፕሮግራም የጀመረው፡፡

ያንብቡት…

FH ኢትዮጵያ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳለዉገለፀ

ሀምሌ 29/2ዐዐ9 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፤የግብርናና የተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ መምህራን፣ የአልሙናይ ኢንዱስትሪ ትስስር እና የፋርም ዳይሬክቶሬቶች እና ባለሙያዎች በተገኙበት በባምባሲ ወረዳ ባሉ ሁለት ቀበሌዎች ላይ FH ኢትዮጵያ በሰጣቸዉ ስልጠና መሰረት የቁጥብ እርሻ ልማትን ተገባራዊ ያደረጉ አርሶ አደሮች ማሳ ጉብኝት አድርጓል፡፡ 

ያንብቡት…

The Universiyty Provides Deliverology Training for all Level Leaders
The Universiyty provided one day training for the presidents, College Deans , directors ,coordinators and department heads on August 15/2009 E.C. The objective of the training was to introduce the new concept of deliverology, higher education targets on deliverology as well as what is planning in deliverology and how it implements.
read more...

Assosa University’s Bamboo seedling plantation

The month of August is the commemorating month of the late Prime Minister Meles Zenawi death in the country level.

FH ኢትዮጵያ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳለዉገለፀ

ሀምሌ 29/2ዐዐ9 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፤የግብርናና የተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ መምህራን፣ የአልሙናይ ኢንዱስትሪ ትስስር እና የፋርም ዳይሬክቶሬቶች እና ባለሙያዎች በተገኙበት በባምባሲ ወረዳ ባሉ ሁለት ቀበሌዎች ላይ FH ኢትዮጵያ በሰጣቸዉ ስልጠና መሰረት የቁጥብ እርሻ ልማትን ተገባራዊ ያደረጉ አርሶ አደሮች ማሳ ጉብኝት አድርጓል፡፡ 

                                                                                           የጉብኝቱ ተሳታፊ ቡድን

FH ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል ድርጅት ሲሆን በሀገሪቱ ባሉ አምስት ክልሎች እየተንቀሳቀሰ በዝቅተኛ ኑሮ የሚገኙ አርሶ አደሮችን በቁጥብ እርሻ መሬት ላይ ዘላቂ ልማትን መሰረት በማድረግ  የአመት ፍጆታቸውን እንዲያገኙ የሚያደርግ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው፡፡

FH ኢኢትዮጵያ በሀገር ደረጃ የሚያከናውናቸው ተግባራት ትምህርት ፣ ጤና ፣ ግብርና እና የመንገድ ጥገና ላይ አትኩሮ እየሰራ እንደነበረ ማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከመጣ 17 አመታተን ያስቆጠረ ሲሆን የመጀመሪያ ስራውን የጀመረው በካማሽ ዞን ቦሎጅጋንፎ ወረዳ ነው፡፡ ድርጅቱ አሁንም ደግሞ በባምባሲ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች ላይ ማለትም በአፋፊር በናሬና በመንደር 48 ቀበሌዎች ላይ ከ2ዐዐ8 ዓ.ም ጀምሮ በግብርናው ዘርፍ በኩል  በአርሶ አደሮች አነስተኛ ማሳ መሬትን ተጠቅሞ የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ እያገዘና እየሰራ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ተገልጿል፡፡ ለአርሶ አደረሮቹ በማሳወቅ ያለው የግብርና ዘዴም  mulchting ( በቁጥብ እርሻ ላይ የታጨደ ሳርን መሬት አልብሶ) የአገዳ ሰብልን በቀላሉ ብዙ ሳይለፉ የማምረት ዘዴ እንደሆነ አርሶ አደሮችን አሳምኖ ወደተግባር እንዲገቡ አድር¹ል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ በዝቅተኛ ኑሮ የሚገኙ አርሶ አደሮች የቁጥብ እርሻን መጠቀም ከጀመሩ ጀምሮ የተሻለ ምርትን እንዳስመዘገቡ የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ማቲወስ ቶሎሳ ገልፀዋል፡፡ አርሶ አደሮቹም በተመሳሳይ መልኩ ምርታቸውን እንዳሳደገላቸው ተናግረዋል፡፡

                                                                              በሜልችንግ የተዘራ የቦቆሎ ሰብል

በጉብኝቱ ወቅትም ከዩኒቨርሲቲው ምን ይጠበቃል የሚለው ሀሳቦች ተነስተዋል፡፡ የሚጠበቀውም መሬትን ደጋግሞ በማረስ ከሚመረትበት ዘዴ ውጤታማነቱን በማወዳደርና በምርምር በመደገፍ ተመራማሪዎች ጥቅሙን ለይተው ለተጠቃሚው አርሶ አደር እንዲያስፍፉ ለማድረግ ብሎም አሉታዊ ጎን ካለውም የሚስተካከልበትን መንገድ ለይቶ በማሳየት FH ኢኢትዮጵያ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በጋራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት ያለው በመሆኑ ጎብኝዎችን በአርሶ አደሮች ማሳ እንዲጎበኙ በማድረግ ያለውን ፍለጎት አሳውቋል፡፡ 

                                                         በሜልችንግ የተዘራ የማሽላ ሰብል                             አቶ ማቲወስ ቶሎሳ

የምርምርና ማህበረሰብ  አገልግሎት ም/ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሀይማኖት ዲሳሳ የቁጥብ እርሻ በትልቅ ማሳ ላይ /መሬት/ ማከናወን ይቻላል? በማለት ጥያቄያቸውን ካቀረቡ በ|ላ ለጥያቄያቸው  መልስ በማገኘታቸው ዩኒቨርሲቲዎች በዋናነት ሲቋቋሙ ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን የማህበረሰብ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ለተጠቃሚዎች ማዳረስ ነው፡፡ ስለዚህ FH ኢኢትዮጵያ ዛሬ በተግባር ያሳየን የቁጥብ እርሻ መሬት ለምርምር ስራው ግብአት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ በቀጣይም ይህንን ተግባር ወደዩኒቨርሲቲያችን በመውሰድ በማወያዬት የምናረጋግጠው ነው ብለዋል፡፡ ከFH ኢትዮጵያ ጋር አብረን በቅንጅት የምንሰራ መሆኑን በቁርጠኝነት መግለጽ እወዳለሁ ነው ያሉት፡፡ 

                                                     ዶ/ር ሀይማኖት መልእክት ሲያስተላልፉ

በተጨማሪም የግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ መምህራን በጉብኝቱ ወቅት ያገኘነው ተሞክሮ በጣም ጥሩ እና የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይ ስራችንም አንድ እራሱን የቻለ የምርምር እርዕስ አግኝተንበታል፡፡ ስለዚህ ከFH ኢትዮጵያ ጋር ከጎን በመሆን በምርምር ስራ ተሰማርተን አድሱን የሰብል ማልማት ዘዴ ተግባራዊ  ለማድረግ ዝግጁ ነን ሲሉ አክለው ገልፀዋል፡፡

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሥዕል አዉደ ርዕይ አካሄደ

ዩኒቨርሲቲዉ ከሰኔ 03-05/2009ዓ/ም በባንቡ ፓራዳይዝ ሆቴል ለ2ኛ ጊዜ ለእይታ ያቀረበዉ የሥዕል አዉደ ርዕይ የምረቃ በዓል ያደረገ ሲሆን ሥራዎቹ በፒካሶ የሥዕል አርት ክለብ በሰዓሊ ፋሲል ሙሉጌታ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ፈጠራና ባህል ማዕከል ዳይረክቶሬት ጋር በመተባበር የተሠሩ መሆኑን መገንዘብ ተችለዋል፡፡

የተሰሩት ሥዕሎች በከፊል
አዉደ ርዕዩን የከፈቱት የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሀይማኖት ዲሳሳ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲዉ እንደዚህ አይነት ልዩ ችሎታ ያላቸዉን ተማሪዎች ማጠናከርና እዉቅና መስጠት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዉ ወደ ፊትም ዩኒቨርሲቲዉ ከጎናቸዉ እንደሚቆም ቃል ገብተዋል፡፡ የተሠሩት የሥዕል ሥራዎቹም ጥሩና አበረታች መሆናቸዉን ጭምር ተናግረዋል፡፡

 

ሰዓሊዉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የመካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ ሲሆን ወደዚህ ሙያ የተቀላቀለዉ የ2ኛ ዓመት ተማሪ እያለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ተማሪዉ እስካሁን ለዚህ ሥራ በግሉ ከ ብር 10,000 በላይ እንዳወጣና ለኪነ-ጥበቡ እድገት የዩኒቨርሲቲዉ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡ ይህንን አኩሪ ሥራ ራሱ ባቋቋመዉ ‘’ፒካሶ የሥዕል አርት ክለብ’’ ከሥሩ 750 አባላት በላይ በማሰለፍ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተማሪዉ ጨምሮ ገልፀዋል፡፡ 

ተመልካቹ የሥዕል ሥራዎቹን ሲጎበኙ
አንዳንድ አስተያዬት ሰጪዎች በተማሪ ፋሲል ሙሉጌታ የተሰሩት የሥዕል ሥራዎችን አድንቀዉ ይበልጥ ለማጠናከር የዩኒቨርሲቲዉ ድጋፍ ወሳኝ መሁኑን ገልፀዉ ዩኒቨርሲቲዉ የአርት (ኪነ-ጥበብ) ትምህርት ቤት ቢከፈትላቸዉ ከዚህ የበለጠ መስራት እና ብዙ ተከታዮችን ማፍራት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

  

በአዉደ ርዕይዉ የተሳተፉት አስተያዬት ሲሰጡ